Home Entertainment / መዝናኛ Social Affairs / ልዩ ልዩ ምግብ ቤት ምግብ ለመብላት ሳይሆን አስተናጋጅ ለማየት የሄዱ በልተው ሳይሆን ተበልተው ነው...

ምግብ ቤት ምግብ ለመብላት ሳይሆን አስተናጋጅ ለማየት የሄዱ በልተው ሳይሆን ተበልተው ነው የተመለሱት

መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ

ምግብ ቤት ምግብ ለመብላት
ሳይሆን አስተናጋጅ ለማየት የሄዱ
በልተው ሳይሆን ተበልተው ነው የተመለሱት

በመጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ

ወደ ቤተክርስቲያን ስንመጣ እግዚአብሔርን ብለን እንጂ ሰባኪ እከሌ መጥቷል ብለን ልመጣ እንደማይገባን እንዲህ በማለት መክረውናል፦ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጡ አየለ ከበደ ይሰብካል የሚለውን ትታችሁ እግዚአብሔርን ብላችሁ ኑ። እግዚአብሔር ለእናንተ ትምህርት አያጣም። ሆቴል እሚኬደው አስተናጋጅ ለማየት አይደለም ምግብ ለመብላት እንጂ። አስተናጋጅ ለማየት የሄዱት ወፍረው ሳይሆን ከስተው ነው የመጡት በልተው ሳይሆን ተበልተው ነው የመጡት።

ሰለዚህ ቤተክርስቲያን ስመጡ እንትና ቀደሰ እንትና ይሰብካል ባላችሁ አትምጡ ይሄ የሰነፍ ሰው ጠባይ ነው። እኛ መጣን ቀረን ምን አስጨነቃችሁ። እኛም በሽተኞች ነን እናንተም በሽተኞች ናችሁ የተገናኘነው ሃኪም ቤት ነው ሃኪሙ ደግሞ እግዚአብሔር ነው።

እኛ ትንሽ ቀዥቀዥ ብለን ማብራራት ጀመርን እንጂ ዶክተሩ እግዚአብሔር ነው። ሃኪም ቤታችን ቤተክርስቲያን ናት። አሁን ወደ ቤታችሁ ስትግቡ እንትና ሰብኮ እንትና አስተምሮ አትበሉ እግዚአብሔር ነገረኝ አስተማረኝ በሉ። አስተማሪ ማን ነው? እግዚአብሔር ነው።

ተናጋሪ ማን ነው እግዚአብሔር ነው።

ፈጣሪን ብቻ ያዙ ሌላ ሰው ላይ አትንጠልጠሉ።

እንደው አንዳንድ ሰው አለ በሰርግ ላይ ሙሽራውን ትቶ ሚዜ ላይ የሚያፈጥ። መታየት ያለበት እኮ ሙሽራ ነው።

የቤተክርስቲያን ሙሽራዋ ማን ነው? ክርስቶስ ነው።

እኛ ምንም ማለት አይደለንም የሠርግ ቤት አውደልዳዮች ነን።

ለቀቅ አድርጉን እኛን በመድኀኒዓለም።

እርሱ ላይ ተጣበቁ ቁስሉ ፈውስ ነው፣ ችንካሩ ፈውስ ነው፣ ሃሞት ኮምጣጤው ፈውስ ነው፣ ግርፋቱ እጅ እግሩ ፈውስ ነው፣ ቃሉ ፈውስ ነው፣ የተሰበረውን ይጠግናል ያለቀሱትን እንባ ያብሳል፣ የወደቁትን ያነሳል፣ የጎደለ ይሞላል። እኔ ምን የጎደለ እሞላላችኋለው ወገኖቼ? ለራሳችን ጎሎብን እኮ እየተሰቃየን ነው ።

እንደነዚህ አይነት መምህር

እግዚአብሔር ያብዛልን አሜን

ካነበብኩት k J ነኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here