Home Entertainment / መዝናኛ Social Affairs / ልዩ ልዩ ፌስቡክ ሌላ ሰው ፎቶ ግራፋችንን ሲጠቀም የሚያሳውቅ አገልግሎት ሊጀምር ነው

ፌስቡክ ሌላ ሰው ፎቶ ግራፋችንን ሲጠቀም የሚያሳውቅ አገልግሎት ሊጀምር ነው

ፌስቡክ ሌላ ሰው ፎቶ ግራፋችንን ያለእኛ እውቅና ገፁ ላይ በመጫን ሲጠቀም የሚያሳውቅ አገልግሎት ሊጀምር ነው።

በዚህም ሌሎች ሰዎች ፎቷችንን ወደ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ለመጫን ሲሞክሩ የፊት መልክ ማረጋገጫን እንደሚጠቀም ነው የገለፀው።

ይህ አሰራር ፎቷችንን ሌሎች ሰዎች ወደ ፌስቡክ ጭነው ለተለያየ አገልግሎት ለመጠቀም ሲሞክሩ ለእኛ በማሳወቅ አስፈላጊውን የግል መብት የማስጠበቅ ስራ እንድንሰራ የሚያስችል ነው።

የማህበራዊ ትስስር ገፅ ኩባንያው ሰዎች የራሳቸውን የግል መብት የሚያስጠብቁበትን ተጨማሪ ቁልፍ እየሰራ መሆኑን ትናንት ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል።

አዲሱ አገልግሎቱ በካናዳ እና በአውሮፓ በቅርቡ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ነው ኩባንያው የገለፀው።

የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለተለያዩ አገልግሎታቸው ማስፈፀሚያ የፊት መልክ ማረጋገጫ የቴክኖሎጂ ቁልፎችን ለመጠቀም ቢያስገድዱም፥ ከፊት ገፅታ የሚወሰዱ ምስሎች እንዴት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ የሚለው የብዙዎች ፍራቻ ነው።

ባሳለፍነው መስከረም ወር አፕል የሞባይል ስልክ አምራች ኩባንያ የአዲሱ የአይፎን 10 (iPhone X) ምርቱን ለመክፈትና ለመዝጋት ፊታቸውን መጠቀም እንደሚችሉ ገልጾ ነበር።

ፌስቡክ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ የፊት መልክ ማረጋገጫ የቴክኖሎጂ ቁልፍን መጠቀም ጀምሯል።

በዚህም ከተወሰነ ጊዜ በፊት ፎቷችንን ታግ(መርጠን የምናጋራው) ሰው መረጃ እንዲደርሰው የፊት መልክ ማረጋገጫን መጀመሩ ይታወቃል።ሆኖም ይህ ግዴታ ሳይሆን አማራጭ ነው።

ኩባንያው የፊት ማረጋገጫ ቁልፎችን ተጠቃሚዎቹ ቁጥጥር እንዲያደርጉባቸው “on/off” የሚል መለያ ለመጨመር አቅዷል።

አሁን ላይ በሚተገብረው አሰራርም የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ፎቷቸውን ሌላ ሰው የማህበራዊ ትስስር ገፅ መጠቀሚያ ፕሮፋይል ፎቶነት ሲጠቀምባቸው በማሳወቅ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመቀነስ አቅዷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here